የመኪና አደጋ ጠበቃ

 

የመኪና አደጋ በገጠመዎት ጊዜ አስቀድመው ማድረግ የሚገባዎት ዝርዝር ጠቃሚ መመሪያዎች፣

፩ኛ) የደረሰብዎት ጉዳት መጠን የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ የሚፈቅድልዎት ከሆነ ፣ በአስቸኳይ የአደጋ እርዳታ 911 ደውለው ይጥሩ። 

የአደጋው መጠን ቀለል ያለ ከሆነ ከሌላ በራሪ መኪና ጋር ተጨማሪ ጉዳት እንዳይገጥምዎት ለፖሊስ ደውለው ከጠሩ በህዋላ መኪናዎ መነዳት የሚችል ከሆነ ፣ የአደጋ ምልክት አብርተው በጥንቃቄ በመንዳት የተጎዳውን መኪናዎትን ከመንገዱ በስተቀኝ መጨረሻ በኩል ወደሚገኘው ክፍት ቦታ ወይም ጠርዝ ላይ ያቁሙ።

ይህንን ከማድረግዎ በፊት ቦታው አመቺ ከሆነ መኪናዎትን ከአደጋው ስፍራ ከማንቀሳቀስዎ በፊት በቅድሚያ በስልክዎ የተለያዩ ፎቶግራፎችን ያንሱ።

 

፪ኛ) በአስቸኳይ የህክምና እርዳታ ይውሰዱ።

  • የአደጋው አይነት ከባድም ቢሆን ቀላል ፣ ወዲያውኑ እርስዎም እና ሌሎች በእርስዎ መኪና ውስጥ ተሳፋሪዎች የነበሩ ሁሉ በአስቸኳይ የህክምና እርዳታ እና የጉዳታቸውን መጠን መመርመር ይኖርባቸዋል። ኤክስ ሬይና ኤም አርአይ መነሳት የደረሰብዎትን የአካል ጉዳት ፈጥኖ ማወቅ ይቻላል።
  • የመኪና አደጋ እንደደረሰብዎት ምንም ህመም ወይም ጉዳት ለጊዜው ላይሰማዎት ይችላል ፣ ነገር ግን ብዙ ጊዜ የመኪና አደጋ የሚያስከትለው የአካል ጉዳት የሚታወቀው ውሎ አድሮ ስለሆነ፣ እርስዎ በዚህ ሳይዘናጉ በአስቸኳይ የህክምና እርዳታ ማግኘት እንዳለብዎት አይርሱ ።
  • በአደጋው ምክነያት ተፈጥረው ነገርግን ወዲያውኑ የህክምና ክትትል ባለማድረግዎ ዘግይተው የሚከሰቱ የአካልጉዳቶች ለጤና አደገኛ ከመሆናቸውም በላይ በአደጋው ለደረሰብዎት የአካል ጉዳት ተመጣጣኝ ካሳ ለማግኘት በሚያደርጉት የህግ ፍትሀዊ ጥያቄ ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር ይችላል።

 

የመኪና አደጋ ጠበቃ

 

፫ኛ) ጠቃሚ መረጃዎችን ያአሰባስቡ።

 

  • በተቻልዎት መጠን በአደጋው ስፍራ ላይ እንዳሉ ተፈላጊ መረጃዎችን ማሰባሰብ ይኖርብዎታል ። መኪናዎትን ከአደጋው ስፍራ ከማንቀሳቀስዎ በፊት የእርስዎንና ሌላውንም መኪና ጨምረው የአደጋውን ሁኔታ በማስረጃነት ሊያሳዩ የሚችሉ ፎቶግራፎች ያንሱ።
  • የሌላውን መኪና አሽከርካሪ ሙሉ ስም ፣ አድራሻ ፣ ስልክና በተለይም የኢንሹራንሱን ስምና የፖሊሲ ቁጥር መውሰድዎን በፍፁም እንዳይረሱ።
  • በመጨረሻም በአደጋው ተጠርቶ/ታ የመጣውን ወይም የመጣችውን የፖሊስ ኦፊሰር ስም እና የባጅ ቁጥር የሚያሳየውን ካርድ መቀበል ይኖርብዎታል።

 

፬ኛ) ሳይዘገዩ ልምድ ያለው የአደጋ ጠበቃ ያነጋግሩ።

 

በመኪና አደጋ ለደረሰብዎት የአካል ጉዳት እና የአእምሮ ስነልቦናዊ ጭንቀት ተመጣጣኝ ካሳ ለማግኘት፣ የህክምና ወጪዎ በእርስዎ ላይ ማናቸውም የገንዘብ እዳ ሳያስከትል፣ ጉዳዩን በፍርድ ቤት ተከታትሎ ፍትህ እንዲያገኙ የሚረዳዎት በአደጋ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የህግ ጠበቃዎች ሊኖርዎት ይገባል።

 

፭ኛ) ከጠበቃ ጋር ከተነጋገረ በኋላ፣ ስለ ደረሰው አደጋ ለራሶት መኪና ኢንሹራንስ ብቻ ደውለው ማሳወቅ ይኖርብዎታል።

  • የመኪና ኢንሹራንስዎ ኤጀንት ስላለዎት የህክምና ወጪ ተጠቃሚነት ዝርዝር ሊገልፅልዎት ይገባል። ነገር ግን የህክምና ምርመራና ክትትልዎን ሳይጨርሱ ከማንኛውም ኢንሹራንስ ወገን ጋር የስምምነት ሠነድ መፈረም አይኖርብዎትም ። ይህንን ከማድረግዎ በፊት የህግ ባለሙያ ማማከር ይኖርብዎታል።
  • በተጨማሪ የጥፋተኛው ነጂን ኢንሹራንስ ኩባንያ በጭራሽ አያነጋግሩ ምክንያቱም ደውለው ለእነሱ ጠቃሚ ለእርስዎ ጎጂ መረጃ መሰብሰብ ልማዳቸው ስለሆነ የእነሱን ጥሪ አይመልሱ ።

 

ሀብተማርያም የሕግ ቢሮ

CALL FOR A FREE CASE EVALUATION

(206) 624-1820​

Personal Injury attorney in Seattle
Personal Injury attorney in Seattle

Shoreline

18820 Aurora Ave N

Suite 206

Shoreline, WA 98133

Phone 206-624-1820​

 

 

Dallas 

12225 Greenville Avenue

Suite 252

Dallas, Texas 75243 

Phone 214-436-6557 

 

 

Washington D.C. 

601 Pennsylvania Ave

Suite 900

Washington D.C., 20004

Phone 1-888-874-2794  

Facebook page for Habtemariam Law Firm
Habtemariam law instagram page
Habtemariam law linkedin page
Super lawyers badge

Congratulations to Neftalem T. Habtemariam who was awarded distinction of 2021 Super Lawyer Rising Stars by Thomas Reuters. Super Lawyers is a rating service of outstanding lawyers from more than 70 practice areas who have attained a high degree of peer recognition and professional achievement.

Rising Stars is a designation of top-rated practicing attorneys selected through extensive evaluation. Only 2.5% of lawyers selected will qualify as Rising Stars, and they must be 40 years old or younger, or have been in practice 10 years or less. Being selected as a Rising Star is a noteworthy honor indicating high performance in the legal field. Congratulations to our 2021 Rising Star, Neftalem T. Habtemariam!

Yakima

402 E Yakima Ave,

Ste 1060

Yakima, WA 98901

Phone ​509-761-6242